ውዷ ሙሽሪት
የእናት ትውስታ
-------------------
እናት በልጇ ሰርግ
ይሄው ዛሬ ላይ ደረስን ፡
ምኑንም ሳናውቀው በየት እንደመጣን፡
የልጄማ ነገር ጭንቅ ብሎኛል፡
ቻውም ብየ ልሸኝኛት ከብዶኛል፡
፡
ውዷ ልጀ ዛሬ ውብ ሆናለች፡
እንደ ጸሀይ ደምቃ ከጨረቃ አምራለች፡
፡
ያው እንግዲህ!፡
፡
ሙሽራ ለመሆን ዛሬን አግኝታለች፡
ዛሬ በኔ ቆርጣ ጥላኝ ትሄዳለች፡
፡
በማታውቀው ቤት ውስጥ ልትኖር ወስና፡
ጥላኝ ልትሄድ ነው በኔ ላይ ጨክና፡
ማታውቀው እጆች እቅፍ ውስጥ ልትገባ፡
ዛሬን ተዘጋጀች ከአበቦች አብባ፡
፡
ትንሽ እንዳሰብኩት ከአንቺ መለየቴን፡
የማያልቅ እንባየ ይሞላዋል አይኔን፡
፡
ውዷ ልጀ አንቺ የአይኔ ማረፍያ፡
እየተመላለስኩ ስሄድ በዚህ በዚያ፡
፡
አልጋሽ ላይ ተኝተሽ ጸጉርሽ ተበትኖ፡
እንቅልፍም ቢጫነኝ በላይ ላይ ሆኖ፡
፡
ሳላይሽ አልተኛም ከ እንቅልፍ ሳልቀሰቅስ፡
ትቼሺም አልሄድም ጸጉርሺን ሳልዳብስ፡
፡
ዛሬ ግን በኔ ላይ ምኑ ፈረደብኝ፡
ሊሊት እና ቅውኑ ባይተዋር ሆነብኝ፡
፡
ዛሬ!
ከምን ግዜም በላይ አይኖቼ ያልነባሉ፡
አገኝሽ ይመስል ውሀን ያፈሳሉ፡
፡
ምክኒያቱን ሳታውቂው አልቀረሺም ልጄ፡
በእቅፌ አስገብቸ አሳድጌሽ በእጄ፡
፡
ደግና ክፋቱን ማላውቀው እንግዳ፡
ይዞብኝ ሊሄድ ነው አውጥቶ ከጓዳ፡
፡
ይህን ሳስብ ውየ ቀና አልኩኝና፡
ጊዜን ወደኋሊት መልሼ እንደገና፡
፡
በሀሳብ ጭልጥ ብየ በትዝታ ስዋኝ፡
ያኔ በአንቺ ግዜ መልሶ ትዝ አለኝ፡
፡
እኔ እንደ አንቺ ሁኘ ሙሽራ ተብየ፡
ሰው ፌት አዙሮ ወደ እኔ እያየ፡
፡
ያችትና ቆንጆ የዛሬ ሙሽሪት፡
ልትለይ እኮ ነው ዛሬ ከእናት አባት፡
፡
እያለ ሲጨፍር ሰው ሲደሰት፡
በአይኔ እየቃኘሁ ሰው ስመለከት፡
፡
አንድ ሰው አጣሁኝ ከቅርቤ የሌለ፡
በልቤ ሚዛን ላይ እንደ ተራራ ያለ፡
፡
እናቴን አጥቸ በአይኔ ስንከራተት፡
እንደ አረገዘ ጉም እንደ ውሃ ሙሊት፡
፡
አይኖቿ ሲያነቡ ከሩቅ ተመለከትኩ፡
ይህን ሰመለከት ለራሴ እንዲህ እልኩ፡
፡
እኔ በማግባቴ ደስተኛ ሁነው፡
ወይም ለባህሉ እናልቅስ ብለው ነው፡
፡
ብየ አሰብኩኝና እኔም ፈገግ አልኩ፡
ትንሽ እንደቆየሁ እኔም ከሀሳብ ባተትኩ፡
፡
ያነን ሁሉ ጊዜ ወደ ኋሊት ሂጀ፡
ሳስበው ቆየሁኝ እኔን በአንቺ ልጀ፡
፡
እናማ የኔ ልጅ !!!፡
፡
ዛሬ እኔ ሳነባ ካየሽ ተመልክተሽ፡
እንዲሁ ብታልፊ ለባህል ነው ብለሽ፡
አንቺም ታይዋለሽ አንድ ልጅሺን ድረሽ
የእናት ትውስታ
-------------------
እናት በልጇ ሰርግ
ይሄው ዛሬ ላይ ደረስን ፡
ምኑንም ሳናውቀው በየት እንደመጣን፡
የልጄማ ነገር ጭንቅ ብሎኛል፡
ቻውም ብየ ልሸኝኛት ከብዶኛል፡
፡
ውዷ ልጀ ዛሬ ውብ ሆናለች፡
እንደ ጸሀይ ደምቃ ከጨረቃ አምራለች፡
፡
ያው እንግዲህ!፡
፡
ሙሽራ ለመሆን ዛሬን አግኝታለች፡
ዛሬ በኔ ቆርጣ ጥላኝ ትሄዳለች፡
፡
በማታውቀው ቤት ውስጥ ልትኖር ወስና፡
ጥላኝ ልትሄድ ነው በኔ ላይ ጨክና፡
ማታውቀው እጆች እቅፍ ውስጥ ልትገባ፡
ዛሬን ተዘጋጀች ከአበቦች አብባ፡
፡
ትንሽ እንዳሰብኩት ከአንቺ መለየቴን፡
የማያልቅ እንባየ ይሞላዋል አይኔን፡
፡
ውዷ ልጀ አንቺ የአይኔ ማረፍያ፡
እየተመላለስኩ ስሄድ በዚህ በዚያ፡
፡
አልጋሽ ላይ ተኝተሽ ጸጉርሽ ተበትኖ፡
እንቅልፍም ቢጫነኝ በላይ ላይ ሆኖ፡
፡
ሳላይሽ አልተኛም ከ እንቅልፍ ሳልቀሰቅስ፡
ትቼሺም አልሄድም ጸጉርሺን ሳልዳብስ፡
፡
ዛሬ ግን በኔ ላይ ምኑ ፈረደብኝ፡
ሊሊት እና ቅውኑ ባይተዋር ሆነብኝ፡
፡
ዛሬ!
ከምን ግዜም በላይ አይኖቼ ያልነባሉ፡
አገኝሽ ይመስል ውሀን ያፈሳሉ፡
፡
ምክኒያቱን ሳታውቂው አልቀረሺም ልጄ፡
በእቅፌ አስገብቸ አሳድጌሽ በእጄ፡
፡
ደግና ክፋቱን ማላውቀው እንግዳ፡
ይዞብኝ ሊሄድ ነው አውጥቶ ከጓዳ፡
፡
ይህን ሳስብ ውየ ቀና አልኩኝና፡
ጊዜን ወደኋሊት መልሼ እንደገና፡
፡
በሀሳብ ጭልጥ ብየ በትዝታ ስዋኝ፡
ያኔ በአንቺ ግዜ መልሶ ትዝ አለኝ፡
፡
እኔ እንደ አንቺ ሁኘ ሙሽራ ተብየ፡
ሰው ፌት አዙሮ ወደ እኔ እያየ፡
፡
ያችትና ቆንጆ የዛሬ ሙሽሪት፡
ልትለይ እኮ ነው ዛሬ ከእናት አባት፡
፡
እያለ ሲጨፍር ሰው ሲደሰት፡
በአይኔ እየቃኘሁ ሰው ስመለከት፡
፡
አንድ ሰው አጣሁኝ ከቅርቤ የሌለ፡
በልቤ ሚዛን ላይ እንደ ተራራ ያለ፡
፡
እናቴን አጥቸ በአይኔ ስንከራተት፡
እንደ አረገዘ ጉም እንደ ውሃ ሙሊት፡
፡
አይኖቿ ሲያነቡ ከሩቅ ተመለከትኩ፡
ይህን ሰመለከት ለራሴ እንዲህ እልኩ፡
፡
እኔ በማግባቴ ደስተኛ ሁነው፡
ወይም ለባህሉ እናልቅስ ብለው ነው፡
፡
ብየ አሰብኩኝና እኔም ፈገግ አልኩ፡
ትንሽ እንደቆየሁ እኔም ከሀሳብ ባተትኩ፡
፡
ያነን ሁሉ ጊዜ ወደ ኋሊት ሂጀ፡
ሳስበው ቆየሁኝ እኔን በአንቺ ልጀ፡
፡
እናማ የኔ ልጅ !!!፡
፡
ዛሬ እኔ ሳነባ ካየሽ ተመልክተሽ፡
እንዲሁ ብታልፊ ለባህል ነው ብለሽ፡
አንቺም ታይዋለሽ አንድ ልጅሺን ድረሽ
0 አስተያየቶች